የዘረኝነት ዛር ሳያንዘረዝራቸው ለአለም በብዙ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያን

Dr., Engineer, Scientist Kitaw Ejigu

The proactive, exemplary, visionary, gifted Ethiopian gem.

ትግሬ ነኝ ፣ ኦሮሞ ነኝ ፣አማራ ነኝ ወይም ደቡብ ነኝ እያልክ ፤ አይደለም እንደነ ቅጣው እጅጉ ጠፈርን(space) ለትመራመር ቀርቶ ፤ ያለህበትን አለም ለመረዳት የራስህንም ህይወት ለማገናዘብ የሚያስችል ጭንቅላት አይኖርህም ። ግራ የገባህ  ፤ ሰላም ያጣህ  ፤ ከዘመኑ ጋር የተጋጨህ እና ወደ ፊት መራመድ የማትችል የተሳሰርክ ፤ በየሄድክበት ከሰዎች ጋር መግባባት የማትችል ከመሆንህ የተነሳ success & accomplishment የራቀህ ሆነህ ታረጃለህ።

ብሄርትኝነትን የማያውቁ ፤ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ተግባብተው  ሰርተው፤ አለምን አጀብ ያስባሉ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች በጥቂቱ(ኢኮኖሚስቶቹን ፣ የቀዶ ጥገና ዶክተሮችን(surgeons)፣ ኢንጂነሮችን …ሌሎችንም በአለም ታዋቂ ምሁራኖቻችንን ሳልጨምር) በጥቂቱ ፡

 

 

1.ቅጣው እጅጉ(Aerospace scientist)

2.ገቢሳ ኢጄታ(geneticist)-World food prize ተሸላሚ ነው

Young

3.አክሊሉ ለማ(physician)-right livelihoodNational award ተሸላሚ ነው

4.ለገሰ ወልደይሀንስ(horticultural scientist)-Right Livelihood award ተሸላሚ ነው

5.ሶስና ሀይሌ(chemist)- NSF   Investigator Award &  J.B. Wagner Award ተሸላሚ ነች

6.መላኩ ወረደ(Agronomist)-Right livelihood award ተሸላሚ ነው

7.ሰገነት ቀለሙ(pathologist) -Loreal-Uniand award ተሸላሚ ነች

8.ዮሀንስ ሀይለስላሴ(paleoanthropologist)

9.ሰለሞን ቢልልኝ (physicist)- American presidential award ከ ኦባማ ተሸላሚ ነው

10.በፀጋው ታደለ (mathematician and software engineer)

gebisa eijeta

The renowned academician and researcher Gebissa Eijeta; a WFP award winner.

 

እንጂነር በፀጋው ታደለ ገና ሳይንቲስት ባይሆንም እንኳ ፤ የቅርብ ትውልድ ስለሆነ ትንሽ ስለሱ እንበል።  ገና ከኮሌጅ ሳይወጣ ፣ የአሜሪካ ፕሬዝደንትን(ኦባማን) በብቃቱ ያስደመመ ፤ በታዋቂው ሞርሀውስ ኮሌጅ የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የመመረቂያ ንግግር (valedictorian speech) ያደረገ ወጣት ነው።

በፀጋው ገና ሳይመረቅ ትምህርት ላይ እያለ የብልጌት በሆነው ግዙፍ ድርጅት (microsoft) ፤ ጠይቆ ሳይሆን ተጠይቆ የስራ ኮንትራት የፈረመ  ሊቅ ወጣት ነው። ፕሬዝደንት ኦባማ በፀጋውን ከራሳቸው ጋር ሲያመሳስሉ  “ይህ የምታዩት በአካሉ ቀጭን የሆነ እና አስቂኝ ስም(ያልተለመደ ስም)  ያለው ሰው (the skinny guy with funny name)  ገና ተአምር ይሰራል ” ነበር ያሉት።

እውነተኛ እውቀት ካለህ(ከተራ ሰዎች ስትልቅ) ፤  በጎሳ እና በዘር አትጠብም ፤ ቁጥር(እውቀት) እንጂ ዘር አትቆጥርም። ስራህ(መጠራትህ) ለአለም ህዝብ ሁሉ እንጅ ለአንድ ቀበሌ ወይም ጎሳ ወይም ብሄረሰብ ብቻ አይደለም። ከየትኛውም የሀገርህም ሆነ የአለም ህዝብ/ዘር/ብሄረሰብ/ ጋር አብረህ ለመስራት እና ለመማማር የተዘጋጀህ መሆን አለብህ። እያንዳንዱ አላማ ያለው ሰው ያልተነበበ መፅሀፍ መሆኑን አትዘንጋ።

“ዘርን ከዘር ለመለየት ለመለየትማ (ለዘር ቆጠራ) ፤  ወደ ዩኒቨርሲቲ ወደ ትምህርት ቤት ሳይሆን ወደኔ እህል ጎተራ ግባ።” ይል ነበር ገበሬው አያቴ።ምክንያቱም አማራ ልሁን ፣ትግሬ ልሁን ፣ኦሮሞ ልሁን ፣ አፍሪካ ልሁን ፣ አውሮፓ ልሁን ብሎ መርጦ የተፈጠረ ወይም የተወለደ የለም። እግዚአብሔር ስለፈቀደ እንጅ አንተ መርጠህ አይደለም ያለህበት ቤተሰብ፣ከተማ ፣ወረዳ፣ክልል ፣ ብሄረሰብ ውስጥ የተወለድከው/የተፈጠርከው።

ኢትዮጵያ የገዛ ምሁራኖቻችን ሳትፈራ እና ሳታርቃቸው ፤ወደ ጉያዋ አስገብታ በብቃት የምትጠቀምበትን  ዘመን እና ልጆቿን ተጠቅማ ከዶላር ልመና እና ከስደት የምትወጣበት ዘመንን ያምጣልን ቸሩ ። ደግሞ ይመጣል በእርግጠኛነት ። ከቦንጋ ገጠር ወጥቶ የአለም ቁንጮ ሆኖ ፤ የኢትዮጵያውንን ስም  በጥበቡ ያስጠራው ፤ የሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው እጅጉን ነብስ ይማር ፤ ለቤተሰቦቹም መፅናናት ይሁን።

Source: A dear friend’s facebook comment

Advertisements