ወያኔ የአዲስ አበባን ገጽታ ሊያመሳቅለው ቀጠሮ ይዟል ይለናል አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ

አዲስ አበባ ብሄራዊበነገው እለት ወያኔ በሚያደርገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ፣ ነባሪያዊ፣ መጻኢ እድል ፈንታ ለመቅየርና ህዝብን በህዝብ ላይ ለማስነሳት የመጨረሻ ጥይት ይተኩሳል ተባለ
ከእንግዲህ የአዲስ አበባ ስም ፊንፊኔ ሲባል፣ ታሪኳ በሙሉ ነበረ ይሆናል::
በዚህ አያበቃም፣ ከኦሮሞ ውጪ እንደዚህ ቀደሙ ማንም በነጻነት አይመላለስባትም:: ሁሉንም ህዝብ የሚያግባባው የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ አማርኛም በከተማዋ አይነገርም፣ ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል መጥቶ ከተማዬ፣ቤቴ ብሎ የሚኖር ሁሉ ከነገ ጀምሮ ቤትህ አይደለም፣ ይህ ይኦሮሞ ቤት ብቻ ነው ይባላል::
እንድከዚህ ቀደሙ መገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ሽሮሜዳ፣መርካቶ፣ ፒያሳ የሚባሉ መጠርያዎች አይኖሩም የያንዳንዱ ሰፈር ስም ይቀየራል፣ ካስፈለገም ስምህ ይቀየራል፣ መሬት ከፈለክ ስምህ ይኦሮሞ መሆን አለበት።
የከተማዋ መስራችና ኣሳዳጊ የነበረው የአማራ ህዝብ አፍንጫህን ላስ ይባላል::

እንደሚታወቀው ከ60% በላይ የሆነው የከተማዋ ነዋሪና ካስፈለገም ባለቤት የሆነው የአማራው ህዝብ በከተማዋ ከ19% በታች በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ተጽኖ ስር ሊወድቅና ፊኒፊኔያዊ አፓርታይድ ሊካሄድ እንድሆነ የአለምነህ ዋሴ ምንጨ የሆነው ከፍተኛ ባለስልጣን ገለጿል::
እንደሚታወሰው ከተወሰኑ ወራቶች በፊት በኦህዴድ ኣማካኝነት ረቅቆ አፈትልኮ ወጣ የተባለው በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም አዋጅADDIS-ABABA የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ የነበረ ሲሆን፣ ህዝቡ ከፍተኛ ትቃውሞ ማሰማቱ አይዘነጋም፣ ሆኖም ወያኔ ኢሃዴግ ብምን ታመጣለህ ንቀት ነገ እውን ሊያደርገው ነው::

ከአመታት በኋላ የአዲስ አበባው የመታወቂያ ላይ ብሄር ጉዳይ አሁን ተገለጠልን፣ አዲስ አበባን ዳግማዊት ሩዋንዳ ሊያደርጓት ነው
ታድያ የአዲስ አበባ ህዝብ ምን ቀረኝ ብለህ ምን ትጠብቃለህ?

Advertisements

የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ውጥረት እንደቀጠለ ነው

 
ኢሳያስ አፈወርቂየኤርትራው ፕሬዝደንት ኣቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በማያገባት ገብታ ሰላማችንን የነሳችን የርጎ ዝንቧ አሜሪካን ነች እንጂ እኛ ወንድማማች ህዝብ ነን:: አህያ ከአህያ ቢራገጥ ጥርስ ዘይዋለቅም እንዲሉ፣ ኢሳያስ አፈወርቂም ከረጅም አመታት በኋላ ስልሁለቱ ህዝቦች አንድነት ሲናገሩ ተደምጠዋል
አቶ ኢሳያስ ይህንን ያሉት ለመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት አባል ሃገራት በተናጠል “የፍትህ ያለህ” ሲሉ የቅሬታ ደብዳቤያቸውን ማስግባታቸውን ተከትሎ ነው
ወትሮም እንኳን ተቋስሎ ተኳርፎ የማይሆንለትን ህዝብ ልማይረባ የፖለቲካ ትርፍ ያበጣበጡት የሁለቱ ሃገራት ወመኔ ፖለቲከኞች አሁን አሁን ኩርፊያ ሰባሪ አነጋጋሪ ፍለጋ ዳር ዳር ማለቱን ይዘውታል::
የኤርትራው ፕሬዝዳንት፣ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት በተወሰነው መልኩ የድንበር ማካለሉ እንዳይከናውን ያደረገችው አሜሪካ ነች ሲሉ በነገረ ሸንቆጥ ቢያደርጉም ሰሚ አጥተዋል::

ኢትዮጵያዊቷ በአሜሪካን ኤምባሲ ውስጥ በወሲብ ባርነት ስትሰቃይ ኖራለች

በጃፓን የአሜሪካን ኤምባሲ

ኢትዮጵያዊቷ ሴት ስትሰቃይበት የነበረበት ሀንጻ፣ በጃፓን የአሜሪካን ኤምባሲ

በአንዲት የአሜሪካን ኤምባሲ ዲፕሎማት ባል ለረዥም ጊዜያት በወሲብ ባርነት ስትሰቃይ የነበረችው ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ከረጀም ኣመታት የወንጀል ምርመራ በኋላ ወንጀሉ እንድትፍጸመባት ተረጋገጠ::  ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ ይፈጸምባት እንደነበርና በሳምንት ለ 80 ሰዓታት ያሰሯት እንደነበርም ገልጻለች::
ሆኖም በወቅቱ በቂ ማስረጃ እንደሌለውና ክስ ሊመሰርት እንድማይችል የገለጸው የአሜሪካኑ የፍትህ ዲፓርትመንት የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ራስል ሃዋርድ ከሞተ በኋላ በ 2012 ምርመራ ማድረግ መጀመሩን ገልጾ እንደነበር አይዘነጋም::
ምንም እንኳ የምርመራና የፍትህ ሂደቱ ቢዘገይም፣ ያአሜሪካን ፍትህ ዲፓርትመንት በካሳነት 3.3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለኢትዮጵያዊቷ ተጠቂ ፈርዶላታል::
ራስል ሃዋርድ በኢትዮጵያዊቷ ላይ ወንጀሉን የፈጸመወ በ 2009 በጃፓን ቶኪዮ በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ውስጥ እንደነበር ተገልጿል::
ራስል ሃዋርድ፣ የ ሊንዳ ሃዋርድ ባለቤት ፣ ባለቤቱ ብመካከለኛው ምስራቅ በስራ ላይ እያለችና ኣብራው እየኖረች መሰልወ ነጀሎችን በየመን በሚኖሩ አራት የተለያዩ ሴቶች ላይም ፈጽሞ እንደነበር ተረጋግጧል::
የዜናው ምንጭ: news.com.au ነው::

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
http://www.news.com.au/national/australian-husband-of-diplomat-kept-ethiopian-girl-as-sex-slave-and-abused-four-maids/news-story/ddc186d888b1ced16d7469f97fe16590