Posted in Ethiopia, Famine, Society

በኢትዮጵያ በሰኔ ወር መጨረሻ 7.8 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ረሃብ ይጋለጣል

a-drought-crisis-in-ethiopiaኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ 7.8 ሚሊዮን ሰዎች የምታደረገው የምግብ እርዳታ በተያዘው ወር መጨረሻ ሊያልቅባት ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ::
በዓለማችን ላይ እየተፈጠሩ ባሉ የተለያዩ ችግሮች ምክንያት ለጋሽ ሃገራትና ድርጅቶች እየተዳከሙና እየተሰላቹ መምጣታቸውን የገለጸው የመንግስታቱ ድርጅት፣ የረሃብ ቀጠናው፣ማለትም ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ እንዲሁም የሰሜን ምስራቃዊ የናይጄሪያ ክፍል ከፍተኛ ረሃብ ሊፈጠር እንደሚችል ገለጿል::
ያለፉትን ሁለት አመታት 381 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድቢያለው ስጋት የለብኝም ያለው የወያኔ መንግስት የቋጠረው ገንዘብ እንዳለቀበትና እጆቹን ወደ ለጋሽ ሃገራትና ድርጅቶች ለመዘርጋት እንደተገደደም የመንግስታቱ ድርጅት አሳውቋል::
የአለም ምግብ ፕሮግራም እና ህጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ቺልድረን)አመራሮቸ በሰኔ ወር መጨረሻ በመጋዘን ያለው ምግብ ሲያልቅ ምን እንደምናደርግ አናውቅም፣ መላው ጠፍቶናል ብለዋል::ethiopia famine