ቀዝቃዛው ጦርነት በኢትዮጵያ

cold war in ethiopia.pngዝብርቅርቅ፣ ዥንጉርጉር፣ ብትንትን ያለው ጸረ ወያኔ ይሁን፣ ጸረ ኢትዮጵይ ይሁን፣ ኣማራዊ፣ ኦሮሚያዊ፣ ጉራጌያዊ፣ ጋምብይላዊ ብቻ መላ ቅጡ የጠፋው ትግል ይሁን ፍትጊያ ያለየለት የሐበሻ ምድር ቀዝቃዛ ጦርነት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከተጀመረ ሰነባበተ።
እናም የፌስቡክ ጦረኞች የሚያደርጉት እልህ ኣስጨራሽ ጦርነት ወኔ የተሞላበት፣ ብሶት የወለደው መሆኑ ጨቓኙን ስራት ኣሽቀንጥሮ እስኪጥል ድረስ ፋታ የማይሰጥ መሆኑ ይበል ያሰኛል።

ሆኖም ይህን የመሰለ ቆራጥነት የሞላበት አለኝ የሚለውን ግብአት ሁሉ በከንቱ ሲያባክን፣ ኣቅጣጫ ሳይኖረው ወይንም ኢላማው የተንሻፈፈ ሆኖ ማየት ያሳዝናል፣ያበሳጫል፣ ያማል። የኣብዛኛው ኢላማ የጎንዮሽ ሆኖ እርስ በርስ እየተፋጀ ይገኛል።

ሃገራዊ ራእይ ያለው ጠፍቶ እርስ በርሱ የሚጫረስ ጎታች በዝቷል። ዋናውን አገራዊ ጠላት ወያኔን ትቶ የርስ በርስ ጦርነቱ ለገላጋይ ኣስቸግሯል።
የኣብዛኛው የፌስቡክ ጦረኛ የሰላ ይሁን የዶለዶመ፣ ብቻ ወያኔን የሚያቆስል፣ ብእሩን የጋራ ጠላታችን ወያኔ ላይ በመምዘዝ ፈንታ፣ ይሉቁንም አንዱ አንዱን እያደማ እርስ በርስ እየትጫረሰ ጭራቁ ወያኔ ከቁስሉ እንዲያገግም እድል እየተሰጠው ይገኛል::

ኢትዮጵያን፣ ወይንም አንዳንዶቹ እንደሚሉት አማራን፣ወይም ኦሮሞን ወይም ሶማሌን፣ቤንሻንጉልን ከጨቋኙ ወያኔ መዳፍ ፈለቅቆ ማውጣት የሚቻለው የተባበረ ክንድ ሲኖር ብቻ ነው::ከዚ በስተቀር፣ የጎንዮሹ ጡጫ ለኋላ ቀን ቂም ማትረፊያ ስለሆነ ሁሉም የትግሉ አካል ነኝ የሚል ግለሰብም ሆነ ቡድን ፍትጊያውን ትቶ የብእሩንም ሆነ የጠብመንጃውን አፈሙዝ ወደወያኔ ላይ ብቻ ቢያደርግ መልካም ነው::
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ውጪ ያለና የምድሪቱን ሰላም የናፈቀ፣ የነጻነት አየር የጠማው፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ደጃፍ በመሄድ መቆሚያ መቀመጫ ማሳጣት፣ በአለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ደጃፍ በመሄድ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ፣ በንደነዚህ አይነት ተጋድሎዎች የወያኔን መሰሬነት መግለጥ ማጋለጥ ያስፈልጋል::
የወያኔን ስርአተ ቀብር የምናስፈጽመው ግን በህዝብ መሃል ወያኔ የፈጠረውን ገደል ማጥበብ ስንችል ብቻ ነው::  በማንኛውም አይነት ሁኔታ የክፉ ዘዋሪዎች መቆስቆሻ ካልታከለበት በስተቀር የትኛውም ህዝብ ለየትኛውም ህዝብ ጠላት ሊሆን አይችልም:: ስለሆነም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ብሄር ለብሄር የሚደረገውን ንቀትና የሚነዛውን ጥላቻ ባለማስተናገድ የኢትዮጵያን ነጻነት እውን እናድርግ::

Advertisements