ወያኔ የአዲስ አበባን ገጽታ ሊያመሳቅለው ቀጠሮ ይዟል ይለናል አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ

አዲስ አበባ ብሄራዊበነገው እለት ወያኔ በሚያደርገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ፣ ነባሪያዊ፣ መጻኢ እድል ፈንታ ለመቅየርና ህዝብን በህዝብ ላይ ለማስነሳት የመጨረሻ ጥይት ይተኩሳል ተባለ
ከእንግዲህ የአዲስ አበባ ስም ፊንፊኔ ሲባል፣ ታሪኳ በሙሉ ነበረ ይሆናል::
በዚህ አያበቃም፣ ከኦሮሞ ውጪ እንደዚህ ቀደሙ ማንም በነጻነት አይመላለስባትም:: ሁሉንም ህዝብ የሚያግባባው የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ አማርኛም በከተማዋ አይነገርም፣ ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል መጥቶ ከተማዬ፣ቤቴ ብሎ የሚኖር ሁሉ ከነገ ጀምሮ ቤትህ አይደለም፣ ይህ ይኦሮሞ ቤት ብቻ ነው ይባላል::
እንድከዚህ ቀደሙ መገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ሽሮሜዳ፣መርካቶ፣ ፒያሳ የሚባሉ መጠርያዎች አይኖሩም የያንዳንዱ ሰፈር ስም ይቀየራል፣ ካስፈለገም ስምህ ይቀየራል፣ መሬት ከፈለክ ስምህ ይኦሮሞ መሆን አለበት።
የከተማዋ መስራችና ኣሳዳጊ የነበረው የአማራ ህዝብ አፍንጫህን ላስ ይባላል::

እንደሚታወቀው ከ60% በላይ የሆነው የከተማዋ ነዋሪና ካስፈለገም ባለቤት የሆነው የአማራው ህዝብ በከተማዋ ከ19% በታች በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ተጽኖ ስር ሊወድቅና ፊኒፊኔያዊ አፓርታይድ ሊካሄድ እንድሆነ የአለምነህ ዋሴ ምንጨ የሆነው ከፍተኛ ባለስልጣን ገለጿል::
እንደሚታወሰው ከተወሰኑ ወራቶች በፊት በኦህዴድ ኣማካኝነት ረቅቆ አፈትልኮ ወጣ የተባለው በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም አዋጅADDIS-ABABA የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ የነበረ ሲሆን፣ ህዝቡ ከፍተኛ ትቃውሞ ማሰማቱ አይዘነጋም፣ ሆኖም ወያኔ ኢሃዴግ ብምን ታመጣለህ ንቀት ነገ እውን ሊያደርገው ነው::

ከአመታት በኋላ የአዲስ አበባው የመታወቂያ ላይ ብሄር ጉዳይ አሁን ተገለጠልን፣ አዲስ አበባን ዳግማዊት ሩዋንዳ ሊያደርጓት ነው
ታድያ የአዲስ አበባ ህዝብ ምን ቀረኝ ብለህ ምን ትጠብቃለህ?

Advertisements

የማይጠይቅ ትውልድ

thought-supressionወያኔ የሰውን አይምሮ ቀይሮ ዶማ ማድረግ ከቻለ፣ ሀሳብን በማፈን አየር በመከልከል ሳይሆን በመሞገትና በመብለጥ በሃሳብ የበላይነቱን ፤ እንዲሁም  ‘የጠባቦቹን’ ጠባብነት ማሳየት ነበረበት እንጂ የአየር ሰኣት በመከልከል፣ የማሰብ ነጻነትን በማፈን መሆን የለበትም::

ህዝቡ ማመዛዘን ይችላል። ወያኔ ግን ከሱ አመለካከት ውጪ ያለው የድሮ ስርአት ናፋቂ አለበለዛም ፀረ ልማት፣ አክራሪ፣ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ሊንድ፣ ብቻ ብዙ ብዙ ኮተት በመኮተት ህዝቡን የማይጠይቅና ፈሪ አድርጎታል። ይህን ሲያደርግ ግን በመጀመርያ ወያኔ ራሱ ፈሪ ስለሆነ ነው። ፍርሃቱን በአፈሙዝ በመሸፈነ ድድብናውን ደግሞ የሀሳብ ነፃነትን በመንጠቅ ለመሸፈን ይሞክራል። የተለየና የተሻለ ሀሳብ ከመጣ፣ ምንም እንኳን ሀገራዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም ወያኔ ሊያስተናግደው ይፈራል። በተቻለውም ፍጥነት እሳቤውንና አሳቢውን ያጠፋቸዋል። ወያኔ የሚያስብና የሚጠይቅ ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ አይወድም። ወያኔ የሀሳብ ጠላት ነው።

ለዛም ነው በመላ ሀገሪቱ ላይ ከአዋቂው ይልቅ አድቃቂው፣ ከጠያቂው ይልቅ ተጠቂው የበዛው። በመላ ሀገሪቱ ሁለት ነገር በስፋት ይስተዋላሉ። አንዱ የሰጋንም የአይምሮንም ጡንቻ ማመንመኛ ሽሻ ቤት፣ ጫት ቤት፣ ጠላ ቤት፣ አረቄ ቤት፣ ጠጅ ቤት ፣ ኮረፌ ቤት ምናምን በቤት ቁጥር ልክ በየመንደሩ ተለቀዋል። እንዲህ ያሉ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩት የወያኔ አድር ባይ አሮጊቶች፣ የመንደር ሴቶች ምናምን በጥቃቅን ተደራጅተው ወጣቱን ያመክኑታል። በነዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለሳለው።Ethiopia-Addis-Ababa-Chi-Cha

ሌላው ደግሞ በየመንደሩ በከፈታቸው ‘ወጣት ማእከላት’ ወጣቱ ጡንቻውን እንዲገነባ፣ ህሊናውን እንዲደፍን በማድረግ እንዳይጠይቅ እንዳያስብ፣ እንዳያዝን እንዳይራራ በማድረግ በጨለማ በየመንደሩ በመበተን ማጅራት እያስመታ ማህበረሰቡ በፍርሀት ቆፈን እንዲያዝ በማድረግ፣ እንደ ድሮው ጎረቤት እንዳያመሽ፣ ስለ ሀገር ስለመንደሩ እንዳያወራ፣ ማጅራት መቺ በመፍራት በጊዜ እንዲገባ በማድረግ ህዝቡን የማይጠይቅ ፈሪ አድርጎታል።

ወያኔ በወንበሩ ላይ ለመቆየት የሚችለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብም።

ብቻ በማንኛውም ዘዴ ህዝቡን እንዳይጠይቅ፣ አማራጭ የመረጃ ምንጭ እንዳይኖረው በማድረግ፣ የራሱን ውሸትና የፈጠራ ታሪክ በመንዛት ህዝቡን አደንዝዞታል፤ ይህንንም አጠናክሮ እየቀጠለበት ነው።