የዘረኝነት ዛር ሳያንዘረዝራቸው ለአለም በብዙ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያን

Dr., Engineer, Scientist Kitaw Ejigu

The proactive, exemplary, visionary, gifted Ethiopian gem.

ትግሬ ነኝ ፣ ኦሮሞ ነኝ ፣አማራ ነኝ ወይም ደቡብ ነኝ እያልክ ፤ አይደለም እንደነ ቅጣው እጅጉ ጠፈርን(space) ለትመራመር ቀርቶ ፤ ያለህበትን አለም ለመረዳት የራስህንም ህይወት ለማገናዘብ የሚያስችል ጭንቅላት አይኖርህም ። ግራ የገባህ  ፤ ሰላም ያጣህ  ፤ ከዘመኑ ጋር የተጋጨህ እና ወደ ፊት መራመድ የማትችል የተሳሰርክ ፤ በየሄድክበት ከሰዎች ጋር መግባባት የማትችል ከመሆንህ የተነሳ success & accomplishment የራቀህ ሆነህ ታረጃለህ።

ብሄርትኝነትን የማያውቁ ፤ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ተግባብተው  ሰርተው፤ አለምን አጀብ ያስባሉ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች በጥቂቱ(ኢኮኖሚስቶቹን ፣ የቀዶ ጥገና ዶክተሮችን(surgeons)፣ ኢንጂነሮችን …ሌሎችንም በአለም ታዋቂ ምሁራኖቻችንን ሳልጨምር) በጥቂቱ ፡

 

 

1.ቅጣው እጅጉ(Aerospace scientist)

2.ገቢሳ ኢጄታ(geneticist)-World food prize ተሸላሚ ነው

Young

3.አክሊሉ ለማ(physician)-right livelihoodNational award ተሸላሚ ነው

4.ለገሰ ወልደይሀንስ(horticultural scientist)-Right Livelihood award ተሸላሚ ነው

5.ሶስና ሀይሌ(chemist)- NSF   Investigator Award &  J.B. Wagner Award ተሸላሚ ነች

6.መላኩ ወረደ(Agronomist)-Right livelihood award ተሸላሚ ነው

7.ሰገነት ቀለሙ(pathologist) -Loreal-Uniand award ተሸላሚ ነች

8.ዮሀንስ ሀይለስላሴ(paleoanthropologist)

9.ሰለሞን ቢልልኝ (physicist)- American presidential award ከ ኦባማ ተሸላሚ ነው

10.በፀጋው ታደለ (mathematician and software engineer)

gebisa eijeta

The renowned academician and researcher Gebissa Eijeta; a WFP award winner.

 

እንጂነር በፀጋው ታደለ ገና ሳይንቲስት ባይሆንም እንኳ ፤ የቅርብ ትውልድ ስለሆነ ትንሽ ስለሱ እንበል።  ገና ከኮሌጅ ሳይወጣ ፣ የአሜሪካ ፕሬዝደንትን(ኦባማን) በብቃቱ ያስደመመ ፤ በታዋቂው ሞርሀውስ ኮሌጅ የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የመመረቂያ ንግግር (valedictorian speech) ያደረገ ወጣት ነው።

በፀጋው ገና ሳይመረቅ ትምህርት ላይ እያለ የብልጌት በሆነው ግዙፍ ድርጅት (microsoft) ፤ ጠይቆ ሳይሆን ተጠይቆ የስራ ኮንትራት የፈረመ  ሊቅ ወጣት ነው። ፕሬዝደንት ኦባማ በፀጋውን ከራሳቸው ጋር ሲያመሳስሉ  “ይህ የምታዩት በአካሉ ቀጭን የሆነ እና አስቂኝ ስም(ያልተለመደ ስም)  ያለው ሰው (the skinny guy with funny name)  ገና ተአምር ይሰራል ” ነበር ያሉት።

እውነተኛ እውቀት ካለህ(ከተራ ሰዎች ስትልቅ) ፤  በጎሳ እና በዘር አትጠብም ፤ ቁጥር(እውቀት) እንጂ ዘር አትቆጥርም። ስራህ(መጠራትህ) ለአለም ህዝብ ሁሉ እንጅ ለአንድ ቀበሌ ወይም ጎሳ ወይም ብሄረሰብ ብቻ አይደለም። ከየትኛውም የሀገርህም ሆነ የአለም ህዝብ/ዘር/ብሄረሰብ/ ጋር አብረህ ለመስራት እና ለመማማር የተዘጋጀህ መሆን አለብህ። እያንዳንዱ አላማ ያለው ሰው ያልተነበበ መፅሀፍ መሆኑን አትዘንጋ።

“ዘርን ከዘር ለመለየት ለመለየትማ (ለዘር ቆጠራ) ፤  ወደ ዩኒቨርሲቲ ወደ ትምህርት ቤት ሳይሆን ወደኔ እህል ጎተራ ግባ።” ይል ነበር ገበሬው አያቴ።ምክንያቱም አማራ ልሁን ፣ትግሬ ልሁን ፣ኦሮሞ ልሁን ፣ አፍሪካ ልሁን ፣ አውሮፓ ልሁን ብሎ መርጦ የተፈጠረ ወይም የተወለደ የለም። እግዚአብሔር ስለፈቀደ እንጅ አንተ መርጠህ አይደለም ያለህበት ቤተሰብ፣ከተማ ፣ወረዳ፣ክልል ፣ ብሄረሰብ ውስጥ የተወለድከው/የተፈጠርከው።

ኢትዮጵያ የገዛ ምሁራኖቻችን ሳትፈራ እና ሳታርቃቸው ፤ወደ ጉያዋ አስገብታ በብቃት የምትጠቀምበትን  ዘመን እና ልጆቿን ተጠቅማ ከዶላር ልመና እና ከስደት የምትወጣበት ዘመንን ያምጣልን ቸሩ ። ደግሞ ይመጣል በእርግጠኛነት ። ከቦንጋ ገጠር ወጥቶ የአለም ቁንጮ ሆኖ ፤ የኢትዮጵያውንን ስም  በጥበቡ ያስጠራው ፤ የሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው እጅጉን ነብስ ይማር ፤ ለቤተሰቦቹም መፅናናት ይሁን።

Source: A dear friend’s facebook comment

Advertisements

ወያኔ የአዲስ አበባን ገጽታ ሊያመሳቅለው ቀጠሮ ይዟል ይለናል አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ

አዲስ አበባ ብሄራዊበነገው እለት ወያኔ በሚያደርገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ፣ ነባሪያዊ፣ መጻኢ እድል ፈንታ ለመቅየርና ህዝብን በህዝብ ላይ ለማስነሳት የመጨረሻ ጥይት ይተኩሳል ተባለ
ከእንግዲህ የአዲስ አበባ ስም ፊንፊኔ ሲባል፣ ታሪኳ በሙሉ ነበረ ይሆናል::
በዚህ አያበቃም፣ ከኦሮሞ ውጪ እንደዚህ ቀደሙ ማንም በነጻነት አይመላለስባትም:: ሁሉንም ህዝብ የሚያግባባው የሃገሪቱ የስራ ቋንቋ አማርኛም በከተማዋ አይነገርም፣ ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል መጥቶ ከተማዬ፣ቤቴ ብሎ የሚኖር ሁሉ ከነገ ጀምሮ ቤትህ አይደለም፣ ይህ ይኦሮሞ ቤት ብቻ ነው ይባላል::
እንድከዚህ ቀደሙ መገናኛ፣ አራት ኪሎ፣ ሽሮሜዳ፣መርካቶ፣ ፒያሳ የሚባሉ መጠርያዎች አይኖሩም የያንዳንዱ ሰፈር ስም ይቀየራል፣ ካስፈለገም ስምህ ይቀየራል፣ መሬት ከፈለክ ስምህ ይኦሮሞ መሆን አለበት።
የከተማዋ መስራችና ኣሳዳጊ የነበረው የአማራ ህዝብ አፍንጫህን ላስ ይባላል::

እንደሚታወቀው ከ60% በላይ የሆነው የከተማዋ ነዋሪና ካስፈለገም ባለቤት የሆነው የአማራው ህዝብ በከተማዋ ከ19% በታች በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ተጽኖ ስር ሊወድቅና ፊኒፊኔያዊ አፓርታይድ ሊካሄድ እንድሆነ የአለምነህ ዋሴ ምንጨ የሆነው ከፍተኛ ባለስልጣን ገለጿል::
እንደሚታወሰው ከተወሰኑ ወራቶች በፊት በኦህዴድ ኣማካኝነት ረቅቆ አፈትልኮ ወጣ የተባለው በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም አዋጅADDIS-ABABA የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ የነበረ ሲሆን፣ ህዝቡ ከፍተኛ ትቃውሞ ማሰማቱ አይዘነጋም፣ ሆኖም ወያኔ ኢሃዴግ ብምን ታመጣለህ ንቀት ነገ እውን ሊያደርገው ነው::

ከአመታት በኋላ የአዲስ አበባው የመታወቂያ ላይ ብሄር ጉዳይ አሁን ተገለጠልን፣ አዲስ አበባን ዳግማዊት ሩዋንዳ ሊያደርጓት ነው
ታድያ የአዲስ አበባ ህዝብ ምን ቀረኝ ብለህ ምን ትጠብቃለህ?

የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ውጥረት እንደቀጠለ ነው

 
ኢሳያስ አፈወርቂየኤርትራው ፕሬዝደንት ኣቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በማያገባት ገብታ ሰላማችንን የነሳችን የርጎ ዝንቧ አሜሪካን ነች እንጂ እኛ ወንድማማች ህዝብ ነን:: አህያ ከአህያ ቢራገጥ ጥርስ ዘይዋለቅም እንዲሉ፣ ኢሳያስ አፈወርቂም ከረጅም አመታት በኋላ ስልሁለቱ ህዝቦች አንድነት ሲናገሩ ተደምጠዋል
አቶ ኢሳያስ ይህንን ያሉት ለመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት አባል ሃገራት በተናጠል “የፍትህ ያለህ” ሲሉ የቅሬታ ደብዳቤያቸውን ማስግባታቸውን ተከትሎ ነው
ወትሮም እንኳን ተቋስሎ ተኳርፎ የማይሆንለትን ህዝብ ልማይረባ የፖለቲካ ትርፍ ያበጣበጡት የሁለቱ ሃገራት ወመኔ ፖለቲከኞች አሁን አሁን ኩርፊያ ሰባሪ አነጋጋሪ ፍለጋ ዳር ዳር ማለቱን ይዘውታል::
የኤርትራው ፕሬዝዳንት፣ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት በተወሰነው መልኩ የድንበር ማካለሉ እንዳይከናውን ያደረገችው አሜሪካ ነች ሲሉ በነገረ ሸንቆጥ ቢያደርጉም ሰሚ አጥተዋል::

ቀዝቃዛው ጦርነት በኢትዮጵያ

cold war in ethiopia.pngዝብርቅርቅ፣ ዥንጉርጉር፣ ብትንትን ያለው ጸረ ወያኔ ይሁን፣ ጸረ ኢትዮጵይ ይሁን፣ ኣማራዊ፣ ኦሮሚያዊ፣ ጉራጌያዊ፣ ጋምብይላዊ ብቻ መላ ቅጡ የጠፋው ትግል ይሁን ፍትጊያ ያለየለት የሐበሻ ምድር ቀዝቃዛ ጦርነት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከተጀመረ ሰነባበተ።
እናም የፌስቡክ ጦረኞች የሚያደርጉት እልህ ኣስጨራሽ ጦርነት ወኔ የተሞላበት፣ ብሶት የወለደው መሆኑ ጨቓኙን ስራት ኣሽቀንጥሮ እስኪጥል ድረስ ፋታ የማይሰጥ መሆኑ ይበል ያሰኛል።

ሆኖም ይህን የመሰለ ቆራጥነት የሞላበት አለኝ የሚለውን ግብአት ሁሉ በከንቱ ሲያባክን፣ ኣቅጣጫ ሳይኖረው ወይንም ኢላማው የተንሻፈፈ ሆኖ ማየት ያሳዝናል፣ያበሳጫል፣ ያማል። የኣብዛኛው ኢላማ የጎንዮሽ ሆኖ እርስ በርስ እየተፋጀ ይገኛል።

ሃገራዊ ራእይ ያለው ጠፍቶ እርስ በርሱ የሚጫረስ ጎታች በዝቷል። ዋናውን አገራዊ ጠላት ወያኔን ትቶ የርስ በርስ ጦርነቱ ለገላጋይ ኣስቸግሯል።
የኣብዛኛው የፌስቡክ ጦረኛ የሰላ ይሁን የዶለዶመ፣ ብቻ ወያኔን የሚያቆስል፣ ብእሩን የጋራ ጠላታችን ወያኔ ላይ በመምዘዝ ፈንታ፣ ይሉቁንም አንዱ አንዱን እያደማ እርስ በርስ እየትጫረሰ ጭራቁ ወያኔ ከቁስሉ እንዲያገግም እድል እየተሰጠው ይገኛል::

ኢትዮጵያን፣ ወይንም አንዳንዶቹ እንደሚሉት አማራን፣ወይም ኦሮሞን ወይም ሶማሌን፣ቤንሻንጉልን ከጨቋኙ ወያኔ መዳፍ ፈለቅቆ ማውጣት የሚቻለው የተባበረ ክንድ ሲኖር ብቻ ነው::ከዚ በስተቀር፣ የጎንዮሹ ጡጫ ለኋላ ቀን ቂም ማትረፊያ ስለሆነ ሁሉም የትግሉ አካል ነኝ የሚል ግለሰብም ሆነ ቡድን ፍትጊያውን ትቶ የብእሩንም ሆነ የጠብመንጃውን አፈሙዝ ወደወያኔ ላይ ብቻ ቢያደርግ መልካም ነው::
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ውጪ ያለና የምድሪቱን ሰላም የናፈቀ፣ የነጻነት አየር የጠማው፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ደጃፍ በመሄድ መቆሚያ መቀመጫ ማሳጣት፣ በአለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ደጃፍ በመሄድ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ፣ በንደነዚህ አይነት ተጋድሎዎች የወያኔን መሰሬነት መግለጥ ማጋለጥ ያስፈልጋል::
የወያኔን ስርአተ ቀብር የምናስፈጽመው ግን በህዝብ መሃል ወያኔ የፈጠረውን ገደል ማጥበብ ስንችል ብቻ ነው::  በማንኛውም አይነት ሁኔታ የክፉ ዘዋሪዎች መቆስቆሻ ካልታከለበት በስተቀር የትኛውም ህዝብ ለየትኛውም ህዝብ ጠላት ሊሆን አይችልም:: ስለሆነም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ብሄር ለብሄር የሚደረገውን ንቀትና የሚነዛውን ጥላቻ ባለማስተናገድ የኢትዮጵያን ነጻነት እውን እናድርግ::

የማይጠይቅ ትውልድ

thought-supressionወያኔ የሰውን አይምሮ ቀይሮ ዶማ ማድረግ ከቻለ፣ ሀሳብን በማፈን አየር በመከልከል ሳይሆን በመሞገትና በመብለጥ በሃሳብ የበላይነቱን ፤ እንዲሁም  ‘የጠባቦቹን’ ጠባብነት ማሳየት ነበረበት እንጂ የአየር ሰኣት በመከልከል፣ የማሰብ ነጻነትን በማፈን መሆን የለበትም::

ህዝቡ ማመዛዘን ይችላል። ወያኔ ግን ከሱ አመለካከት ውጪ ያለው የድሮ ስርአት ናፋቂ አለበለዛም ፀረ ልማት፣ አክራሪ፣ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ሊንድ፣ ብቻ ብዙ ብዙ ኮተት በመኮተት ህዝቡን የማይጠይቅና ፈሪ አድርጎታል። ይህን ሲያደርግ ግን በመጀመርያ ወያኔ ራሱ ፈሪ ስለሆነ ነው። ፍርሃቱን በአፈሙዝ በመሸፈነ ድድብናውን ደግሞ የሀሳብ ነፃነትን በመንጠቅ ለመሸፈን ይሞክራል። የተለየና የተሻለ ሀሳብ ከመጣ፣ ምንም እንኳን ሀገራዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም ወያኔ ሊያስተናግደው ይፈራል። በተቻለውም ፍጥነት እሳቤውንና አሳቢውን ያጠፋቸዋል። ወያኔ የሚያስብና የሚጠይቅ ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ አይወድም። ወያኔ የሀሳብ ጠላት ነው።

ለዛም ነው በመላ ሀገሪቱ ላይ ከአዋቂው ይልቅ አድቃቂው፣ ከጠያቂው ይልቅ ተጠቂው የበዛው። በመላ ሀገሪቱ ሁለት ነገር በስፋት ይስተዋላሉ። አንዱ የሰጋንም የአይምሮንም ጡንቻ ማመንመኛ ሽሻ ቤት፣ ጫት ቤት፣ ጠላ ቤት፣ አረቄ ቤት፣ ጠጅ ቤት ፣ ኮረፌ ቤት ምናምን በቤት ቁጥር ልክ በየመንደሩ ተለቀዋል። እንዲህ ያሉ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩት የወያኔ አድር ባይ አሮጊቶች፣ የመንደር ሴቶች ምናምን በጥቃቅን ተደራጅተው ወጣቱን ያመክኑታል። በነዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለሳለው።Ethiopia-Addis-Ababa-Chi-Cha

ሌላው ደግሞ በየመንደሩ በከፈታቸው ‘ወጣት ማእከላት’ ወጣቱ ጡንቻውን እንዲገነባ፣ ህሊናውን እንዲደፍን በማድረግ እንዳይጠይቅ እንዳያስብ፣ እንዳያዝን እንዳይራራ በማድረግ በጨለማ በየመንደሩ በመበተን ማጅራት እያስመታ ማህበረሰቡ በፍርሀት ቆፈን እንዲያዝ በማድረግ፣ እንደ ድሮው ጎረቤት እንዳያመሽ፣ ስለ ሀገር ስለመንደሩ እንዳያወራ፣ ማጅራት መቺ በመፍራት በጊዜ እንዲገባ በማድረግ ህዝቡን የማይጠይቅ ፈሪ አድርጎታል።

ወያኔ በወንበሩ ላይ ለመቆየት የሚችለውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠብም።

ብቻ በማንኛውም ዘዴ ህዝቡን እንዳይጠይቅ፣ አማራጭ የመረጃ ምንጭ እንዳይኖረው በማድረግ፣ የራሱን ውሸትና የፈጠራ ታሪክ በመንዛት ህዝቡን አደንዝዞታል፤ ይህንንም አጠናክሮ እየቀጠለበት ነው።

የማህበራዊ ድረ ገጾች ከዘጠኝ ወራት እገዳ በኋላ ነጻ ወጡ

Facebook-Guns-03255683743በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ወራት የዘለቀው የማህበራዊ ገጾች እገዳ ከአርብ እለት ምሽት ጀምሮ መለቀቁን የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ::
ካለፉት ኣምስት ኣመታት ወዲህ እየሰፋ የመጣው ህዝባዊ አመጽ ያሰጋው የወያኔ መንግስት ህዝብ በስፋት የሚገለገልባቸውን ማህበራዊ ገጾች ፌስቡክንና ትዊተርን አግዶ ነበር::

logo_twitter_withbird_1000_allblue32
በጎንደርና በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልሎች ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ አመጽ የተጠቀሱት ማህበራዊ ድረ ገጾች በስፋት ጠቅም ላይ መዋላቸው ኣይዘነጋም::
ይሁን እንጂ ማህበረሰቡ የታገዱትን ገጾች በፕሮግዚ ሰብሮ በማለፍ ይጠቀም እንደነበር ይታወቃል::

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
http://www.china.org.cn/world/2017-06/11/content_41005517.htm

የኢትዮጵያ መንግስት የወደብ አክሲዮን ገዛ

ASEB PORT  የአሰብ ወደብ

ታላቋን ትግራይ ለመገንባትሲባል ከኢትዮጵያ የተነጥቀው የአሰብ ወደብ:: A port unfairly snached from Ethiopia for the sake of building The Great Tigray.

የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሌ የሚገኘውን የበርበራ ወደብ በባለቤትነት ለማስተዳደር አክሲዮን መግዛቱ እየተነገረ ነው:: ከናይጄርያ ቀጥሎ በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ወደር ያልተገኘላት ኢትዮጵያ የምታመርታቸውን የኢንዱስትሪ ምርቶች ለአለም አቀፍ ንግድ ለማቅረብ ወደብ ያስፈልገኛል ስትል ማመልከቻ ማስገባቷን የሶማሌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳኣድ ኣሊ ገልጸዋል::

በሶማሌ የሚገኘውን የበርበራ ወደብ ዲፒ ዎርልድ (DP World) የተባለው ታዋቂው የወደብ ኣስተዳደር ኩባንያ የወደቡን 51% ሲይዝ፣ የሶማሊያ መንግስት 30% እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት 19% እንደሚይዝ ታውቋል::
ኢትዮጵያ የራሷ ወደብ ያላት ሃገር ስትሆን በህውሃት ባለስልጣናት ወደቧ ተነጥቆ ለሻቢያ መንግስት መሰጠቱ አይዘነጋም::